“በህብረት ቸለናል” በሚል መሪ ሃሳብ የፓናል ውይይት ተካሄደ - Welcome

Nested Portlets

Asset Publisher

Slide Wed, 12 Aug 2026

Slide Wed, 12 Aug 2026

Slide Wed, 12 Aug 2026

Slide Wed, 12 Aug 2026

Facts about the Dam

× LOCATIONBenishangul-Gumuz region, Ethiopia.
× CONSTRUCTION STARTED:2011 G.C.
×Area: 1,874 sq KM
× RESERVOIR CAPACITY: 74 billion cubic metres

About GERD

Asset Publisher

Asset Publisher

“በህብረት ቸለናል” በሚል መሪ ሃሳብ የፓናል ውይይት ተካሄደ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ነሃሴ 30/2017 ዓ.ም “በህብረት ቸለናል” በሚል መሪ ሃሳብ ሚኒስትሮች፣ የፓርላማ አባላት፣ የጽ/ቤቱ አመራሮች፣  ምሁራን፣ የባለድርሻ አካላት፣ የዲያስፖራ አባላት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦችን ያሳተፈ የፓናል ውይይት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ባዘጋጀው በዚሁ የፓናል ውይይት በታላቁ ህዳሴ ግድብ የ14 ዓመታት የመንግስትና የህዝብ ትግልና ሁለንተናዊ ተሳትፎ፣ የግድቡ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች፣ ግድቡ ለቀጠናዊና ለአፍሪካ አህጉር ያለው አስተዋጽኦና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ቀርበዋል፡፡

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የጽ/በቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አረጋዊ በርሄ (ፒኤችዲ) ለግድቡ ምረቃ ስለበቃን እንኳን ደስ ያላችሁ፤ በኛው ላብ፣ ደም፣ ዕውቀት፣ ገንዘብ፣ ትብብርና አንድነት ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት ለፍሬ አብቅተናል፤ የነጋችንም ተስፋ አለምልመናል ብለዋል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ደዒታ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ የፓናል ውይይቱን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት ያለ ውጪ ሀገራት ብድር በራስ አቅም ሃገራችን ሳትጠበቅ ትልቁን ገድል ፈጽማለች፤ ይህንን ዕውን እንድናደርግ ትልቅ አቅም የሆነንን የአንድነትና የመተባበር እሴት በሌሎች ሃገራዊ የልማት ስራዎችም ላይ ማስቀጠል አለብን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የፓናል ውይይቱን ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር ኮሚቴ ሰብሳቢ የመሩት ሲሆን አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ  የውሃ ሀብት አስተዳደር፣ ድንበር ተሻጋሪና የውሃ ዲፖሎማሲ ምሁር እና አቶ ጌታቸው ግዛው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሄራዊ አረንጓዴ አሻራ ቴክኒክ ኮሚቴ ም/ል ሰብሳቢ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ ከፓናሊስቶቹ ማብራሪያዎች በኋላ በተካሄደው የውይይት ጊዜ በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሃሳቦችና ጥያቄዎችን አንስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በመዝጊያ ንግግራቸው በህዳሴ ግድብ አንድ ዕርምጃ ወደ ፊት ተራምደናል፤ ከፊታችን ብዙ ዕርምጃዎች ይቀሩናል፤ ሌሎች ግድቦች ሌሎች የልማት ስራዎች ይጠብቁናል፤ ይህ የሁሉም ትኩረትና ጉዳይ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 9 results.

About Us

Benefits of the Grand Renaissance Project

At the completion of the project, the average generation of 15,759 Giga watt hours per year will have a significant contribution to the national electricity system. The contribution of this project will be higher to reach the targets set by the rural electrification villages and to increase the supply from 44% to 90%.

The major components of the project

The Grand Ethiopian Renaissances Dam is being constructed for the purpose of generating electricity with total installed capacity of average annual energy production of about 15,759 GWh/yr.

Discharge rate about 1,547 m3/s.

The reservoir area will cover 1,874 square kilometers at full supply level of 640 meters above sea level maximum amd 590 metres minimum.

It has a 1.8 km length and 145 m height Roller Compacted Concrete dam.

Saddle Dam embankment of length 5.2 km and height 50 m.

The total storage volume is 74 billion cubic meters