Asset Publisher

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ከመቸውም ጊዜ በላይ ብሄራዊ ማንነትንና ሀገራዊ ኩራትን የሚያላብስ ነው፡፡

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አመራሮች፣ ሠራተኞችና የክልል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ሀምሌ 25-27 ቀን 2017 ዓ/ም በአፍሪካ ሥራ አመራር የልህቀት ማዕከል ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

ሥልጠናውን የሰጡት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛዲግ አብርሃ እንዳሉት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መገንባት እና መጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ብሎም ለሀገረ-መንግስቱ ከመቸውም ጊዜ በላይ  የብሄራዊ ማንነትንና ሀገራዊ ኩራትን የሚያላብስ መሆኑን ጠቁመዋል።

 

ፕሬዘንዳንቱ፤  የግድብ ታሪካዊ አመጣጥ፣ ጠቀሚታውን እንዲሁም ለሀገረ መንግስት፣ ለሀገረ ብሄርና ለተቋሟት ግንባታ ያለውን ከፍተኛ አሰተዋጽኦ በዝርዝር አብራርተዋል። ግድቡ በመንግስት አመራሮች ቅብብሎሾ ለፍፃሜ መድረሱን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመው፤ ይህም ኢትዮጵያ ጀምሮ የመጨረስ ብቃትንና ባህልን እያዳበረች መምጣቷን ለአለም ያስመሰከረችበት ነው ብለዋል።

የህዳሴ ግድብ የሃይማኖት፣ የብሄር፣ የፖለቲካ አመለካከቶችና ሌሎችንም ልዩነቶች ወደ ጎን በመተው በጋራ ክንድ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሀገራዊ አርማ የሆነ ግድብ ነው። ይህም የሀገራዊና ቀጠናዊ የሀይል ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፤ በአጠቃላይ ለሀገሪቱ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግርን የሚያረጋግጥ ይሆናል ኢሉ አክለዋል፡፡

 

 

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የማንሰራራት ትርክት፣ የአንድነት፣ የዘመናዊነት እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ኩራት መገለጫ ከመሆኑም በላይ የኢነርጂ ሉዓላዊነታቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን ማሳያ ጭምር ነው ብለዋል፡፡ ግድቡ በላይኛውና በታችኛው ተፋሰስ ጸንቶ የቆየውን ታችኞቹ ይጠቀማሉ ላይኞቹ ውሃውን ይልካሉ የሚለውን ትርክት የበጣጠሰ ነው፤ በተለይም ውሃ እያላቸው መጠቀም ላልቻሉ የዓለም ህዝቦች የማንቂያ ደወል ነው ሲሉ ፕሬዘዳንቱ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የኢንጂነሪንግ አቅም እንዲሁም የሀገሪቱ የፖሊሲ፣ የኮሙዩኒኬሽን እና የዲፕሎማሲ ጥረት ትልቅ ማሳያ መሆኑንም ገልፀዋል።