"ተስፋን እንትከል!" - Welcome

Sisällytetyt portletit

Sisältöjulkaisija

Slide ke, 12 elokuuta 2026

Slide ke, 12 elokuuta 2026

Slide ke, 12 elokuuta 2026

Slide ke, 12 elokuuta 2026

Alerts

× LOCATION: Benishangul-Gumuz region, Ethiopia.
× CONSTRUCTION STARTED:2011 G.C.
×Area: 1,874 sq KM
× RESERVOIR CAPACITY: 74 billion cubic metres

Sisällytetyt portletit

Sisältöjulkaisija

Sisältöjulkaisija

"ተስፋን እንትከል!"

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት) የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ-ሀሳብ የአረንጓዴ አሻራ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊና ታሪካዊ አካል የሆነውን ‎የዘንድሮ መርሃ-ግብር በግቢያቸው የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል የተስፋ አሻራቸውን አኑረዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የዘንድሮውን ጨምሮ ባለፉት ዓመታት በዚህ መርሐ ግብር ላይ ጉልህ እንቅስቃሴ በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል።‎ የተተከሉት ችግኞች አብዛኛዎቹ ለምግብነት የሚውሉና አገር በቀል የፍራፍሬ፣ የቅመማ ቅመም፣ ለእንስሳት መኖነት የሚያገለግሉ እና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸው።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወርቁ ጓንጉል ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ገልጸዋል፡፡ አረንጓዴ አሻራ የአገራችንን የከባቢ አየር ደህንነት ለመጠበቅ፣ የደን ሽፋንን ለማሳደግና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በየዓመቱ የሚካሄድ ሀገራዊ እንቅስቃሴ እንደሆነም አቶ ወርቁ ተናግረዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የችግኝ ተከላ ኦረንቴሽን የሰጡት የጽ/ቤቱ የአካባቢ ጥበቃና የተፋሰስ ልማት ከ/ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ መሰረት መለሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅና የደን ሽፋንን ማሳደግ ለሥነ ምህዳር ሚዛን፣ ለአገሪቱ የአረንጓዴ ልማት ራዕይ እንዲሁም ለዘላቂ ቱሪዝም እድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ የሚያስመዘግበው ውጤት ከተፈጥሮ ጥበቃ ባለፈ ለኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል።
ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች ከዚህም በተጓዳኝ በዕለቱ የግቢ የጽዳት ዘመቻ መርሃ-ግብር አከናውነዋል፡፡
"አረንጓዴ አሻራ" የነገዋን ኢትዮጵያ አረንጓዴ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ የትላንት ታሪካችንንና ሀብታችንን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ የማስተላለፊያ አስተማማኝ መከታችን ነው! ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም እንደ ሀገር በአንድ ጀምበር 800 ሚልዮን ችግኞችን ለመትከል የታቀደውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት የራሳችንን ድርሻ እንወጣ የሚለው ወርቃማ መልዕክታችን ነው፡፡
"ተስፋን እንትከል!"

 

Sisältöjulkaisija

— Merkintöjä per sivu
Näytetään tulokset 1 - 5 / 9

About Us

Benefits of the Grand Renaissance Project

At the completion of the project, the average generation of 15,759 Giga watt hours per year will have a significant contribution to the national electricity system. The contribution of this project will be higher to reach the targets set by the rural electrification villages and to increase the supply from 44% to 90%.

The major components of the project

The Grand Ethiopian Renaissances Dam is being constructed for the purpose of generating electricity with total installed capacity of average annual energy production of about 15,759 GWh/yr.

Discharge rate about 1,547 m3/s.

The reservoir area will cover 1,874 square kilometers at full supply level of 640 meters above sea level maximum amd 590 metres minimum.

It has a 1.8 km length and 145 m height Roller Compacted Concrete dam.

Saddle Dam embankment of length 5.2 km and height 50 m.

The total storage volume is 74 billion cubic meters