Asset Publisher

የክረምት በጎ ተግባር

የውሃና ኢነርጂ ሚ/ር እና የተጠሪ ተቋማት አማራሮች በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ ባካሄደው የክረምት በጎ ተግባር ከማህበረሰቡ ምስጋና ተቸራቸው።
ነሃሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ሀዋሳ፣ (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት)
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ ዲላ አፍራራ ቀበሌ ባካሄደው የክረምት በጎ ተግባር መርሃ ግብር ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጨባጭ ጥቅም የሚያስገኙ የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወኑ ከአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና ተችሯቸዋል።

                                                                                                              
በመርሃ ግብሩ የ7 አቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤቶችን የመገንባት ሥራ በአፋጣኝ እንዲጀመር ተደርጓል። በተጨማሪም የአገራዊ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ለማሳካት 5,000 ችግኞች ተተክለዋል።
እንዲሁም በደም እጥረት ምክንያት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሕይወት አደጋዎችን ለመቀነስ በማሰብ የሚኒስቴሩና በተጠሪ ተቋማት አመራሮች በበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ አካሂደዋል።
በትምህርት ዘርፍም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ለ500 ተማሪዎች ለ2019 የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶች፣ ማለትም ደብተር፣ እርሳስ፣ እስክርቢቶ፣ ላጲስ እና መቅረጫ በመለገስ ድጋፍ ተደርጓል።
በተጨማሪም ለአካባቢው ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የሕይወት ልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር በማካሄድ በሀገር ግንባታና በማህበረሰብ አገልግሎት ያላቸውን ሚና ለማጠናከር እንዲሁም የበጎ ፈቃድ ባህል ለማጎልበት የግንዛቤ ሥራ ተከናውኗ ል።                                                                                                                                                      
በአካባቢው የሚኖሩት ወ/ሮ አበራሽ ታመነ፣ ወ/ሮ ሕይወት ጴጥሮስ እና አቶ ታደሰ አብርሃም እንደገለጹት ሚኒስቴሩ ለማህበረሰቡ እያደረገ ያለው በጎ አስተዋፅኦ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን በመግለጽ ለሚኒስቴሩ ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በቀጣይም የመንግሥትን የማህበራዊ ኃላፊነት ፕሮግራሞች በማጠናከር ለማህበረሰቡ ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኙ የበጎ ተግባራትን በስፋት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።